Google Payments የግላዊነት ማስታወቂያ

በGoogle Payments የሚቀርቡ አገልግሎቶች በGoogle Payments የግላዊነት ማስታወቂያ የሚሸፈኑ ናቸው። የGoogle Payments የግላዊነት ማስታወቂያ ዝማኔ ከሴፕቴበር 23፣ 2018 ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል። እዚህ በሚገኘው አገናኝ ላይ የዘመነውን ማስታወቂያ መመልከት ይችላሉ።

ለመጨረሻ ጊዜ የተቀየረው ሜይ 21፣ 2018

Google የግላዊነት መመሪያ እርስዎ በGoogle ምርቶችና አገልግሎቶች በሚጠቀሙበት ጊዜ የግል መረጃዎን እንዴት እንደምንይዘው ያብራራል። Google Payments ለGoogle መለያ ባለቤቶች የቀረበ ሲሆን አጠቃቀምዎም በGoogle የግላዊነት መመሪያ ተገዢ በመሆን ነው። በተጨማሪም፣ ይህ የግላዊነት ማስታወቂያ ለGoogle Payments ልዩ የሆኑ የGoogle የግል ተግባሮችን ያብራራል።

የእርስዎ የGoogle Payments አጠቃቀም በዚህ የግላዊነት ማስታወቂያ የተገለጹትን አገልግሎቶች በበለጠ በሚያብራራው በGoogle Payments የአገልግሎት ውል የሚመራ ነው። በዚህ የGoogle Payments የግላዊነት ማስታወቂያ ውስጥ ያልተብራሩትና በእንግሊዝኛ አብይ ፊደላት የተጻፉት ቃላት በGoogle Payments የአገልግሎት ውል ውስጥ የተገለጸውን ትርጉማቸውን ይይዛሉ።

የGoogle Payments የግላዊነት ማስታወቂያ የGoogle Payment ኩባንያን («GPC») ጨምሮ በGoogle LLC ስር በሚተዳደሩ ድርጅቶች ለቀረቡ አገለግሎቶች ይተገበራል። አገልግሎቱን የሚሰጡ በGoogle የሚተዳደሩ አገልግሎት አቅራቢ ኩባንያዎችን ለማወቅ እባክዎ ከአገልግሎቱ ጋር የቀረበልዎትን የGoogle Payments የአገልግሎት ውል ይመልከቱ።

የምንሰበስበው መረጃ

Google የግላዊነት መመሪያ ውስጥ ከተዘረዘረው መረጃ በተጨማሪ የሚከተሉትንም ልንሰበስብ እንችላለን፦

 • ከሦስተኛ ወገኖች የሚገኝ መረጃ - የሦስተኛ ወገን የማረጋገጫ አገልግሎቶችን ጨምሮ እርስዎን የሚመለከት መረጃ ከሦስተኛ ወገን ልናገኝ እንችላለን። ይህ ከሚያካትታቸው መካከልም በንግድ ቦታዎች ከGoogle Payments ግብይቶች የሚገኙ መረጃዎች፣ የመክፈያ ዘዴ አጠቃቀምዎን የሚመለከቱ መረጃዎች እና በሦስተኛ ወገን የተሰጡ እና ከGoogle Payments ጋር የተገናኙ የእርስዎ መለያዎች፣ ካርድ የሰጠዎት አካል ወይም የገንዘብ ተቋም ማንነት፣ በGoogle Payments መለያዎ ውስጥ ወደሚገኝ ሂሳብ ጥቅም ላይ የሚውል መዳረሻን የሚመለከት መረጃ፣ ከአገልግሎት አቅራቢ ወይም በአገልግሎት አቅራቢ በኩል የሚደረግ ክፍያን የሚመለከት የአገልግሎት አቅራቢ ወይም የከዋኝ መረጃ፣ በዩናይትድ ስቴትስ ሚዛናዊ የክሬዲት ሪፖርት ድንጋጌ ውስጥ ባለው «የሸማቾች ሪፖርት» ትርጓሜ መሰረት የሸማቾች ሪፖርት።
 • እንዲሁም ለሻጮች፣ እርስዎን እና ንግድዎን የሚመለከት መረጃ ከክሬዲት ቢሮ ወይም ከንግድ መረጃ አገልግሎት ልናገኝ እንችላለን።

 • የግብይት መረጃ - ግብይት ለመፈጸም Google Payments ሲጠቀሙ፣ የሚከተሉትን ጨምሮ የተወሰኑ ግብይቱን የሚመለከቱ መረጃዎች ልንሰበስብ እንችላለን፦ ቀንና ሰዓት እና የግብይቱ መጠን፣ የነጋዴው አካባቢ እና መግለጫ፣ ስለተገዙት ሸቀጦችና አገልግሎቶች በሻጭ የተሰጠ መግለጫ፣ ከግብይቱ ጋር እንዲያያዝ የመረጡት ማናቸውም ፎቶ፣ የሻጭ እና የገዢ (ወይም የላኪ እና የተቀባይ) ስሞች እና ኢሜይል አድራሻዎች፣ ጥቅም ላይ የዋለው የመክፈያ ዘዴ አይነት፣ ለግብይቱ በምክንያትነት ያስቀመጡት መግለጫ፣ እንዲሁም ያለ ከሆነ፣ ከግብይቱ ጋር የተያያዘ ቅናሽ።
 • የሰበሰብነውን መረጃ እንዴት እንደምንጠቀምበት

  Google የግላዊነት መምሪያ ውስጥ ከተዘረዘሩት ጥቅሞች በተጨማሪ፣ ለእኛ እና ለGPC ወይም በስራችን ለሚተዳደሩ ሌሎች ድርጅቶች ያቀረቡልንን መረጃ እንዲሁም ስለእርስዎ ከሦስተኛ አካላት የተገኘን መረጃ የGoogle Paymentsን ለደንበኞች አገልግሎት አላማ እንድናቀርብልዎ እና ከመጭበርበር ከመታለል ወይም ከሌሎች መጥፎ ምግባር እንድንጠብቅዎ እንጠቀማለን። በተጨማሪም እንደዚህ አይነት መረጃ ሦስተኛ ወገኖች እንዲያቀርቡልዎት የጠየቋቸውን ምርቶችና አገልግሎቶች ለማቅረብ እንዲችሉ ለማገዝ ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል። እንዲሁም የመለያውን ውሎች በማክበር የቀጠሉ መሆኑን ለማወቅ፣ የወደፊት የGoogle Payments ግብይቶችዎን በተመለከተ ውሳኔ ለመወሰን፣ እንዲሁም በእርስዎ የተጠየቁ የGoogle Payments ግብይቶችን ለሚመለከቱ አግባብነት ያላቸው የንግድ ፍላጎቶች የGoogle Payments መለያዎን ለመገምገም መረጃውን እንጠቀምበታለን።

  የምዝገባ መረጃዎ ከGoogle መለያዎ ጋር በመያያዝ ይቀመጣል እንዲሁም የመክፈያ ዘዴ ምዝገባዎ በGoogle አገልጋዮች ላይ ይቀመጣል። በተጨማሪም፣ የተወሰኑ የውሂብ ክፍሎች በተንቀሳቃሽ መሳሪያዎ ላይ ሊከማቹ ይችላሉ። ያቀረቡትን መረጃ የህግ ሂደትን እና የቁጥጥር ግዴታዎችን ለማክበር ለተራዘመ ጊዜ ልናቆየው እንችላለን።

  የምናጋራው መረጃ

  በሚከተሉት ሁኔታዎች ብቻ የእርስዎን መረጃ ከGoogle ውጭ ላሉ ሌሎች ኩባንያዎች ወይም ግለሰቦች ልናጋራ እንችላለን፦

  ለምሳሌ፣ Google Payments በመጠቀም ግዢ ወይም ግብይት በፈጸሙ ጊዜ፣ ግዢ ለሚፈጽሙለት ወይም ለሚገበያዩት ኩባንያ ወይም ግለሰብ እርስዎን የሚመለከቱ የተወሰኑ የግል መረጃዎችን ልናቀርብ እንችላለን። ይህም በGoogle Play ላይ ግዢ ለመፈጸም Google Payments በሚጠቀሙበት ጊዜ ግዢ ለሚፈጽሙለት ገንቢ የግል መረጃዎን ማጋራትን ያካትታል።

  የተሳታፊ ነጋዴን ጣቢያ ወይም መተግበሪያ ሲጎበኙ፣ በጣቢያዎች ወይም በመተግበሪያዎች ጥቅም ላይ መዋል የማይችሉ ባህሪያትን የማየት እድልዎን ለመቀነስ ነጋዴው እንዲከፍሉት የሚያስችል የGoogle ክፍያዎች መለያ ጥቅም ላይ መዋል ከሚችል የክፍያ ቅጽ ጋር እንዳለዎት ማረጋገጥ ይችላል።

  ለሦስተኛ ወገን ነጋዴ፣ ድር ጣቢያ ወይም ማመልከቻ በቀጥታ የሚያቀርቡት ማንኛውም መረጃ በዚህ የግላዊነት ማስታወቂያ አይሸፈንም። የግል መረጃዎን በቀጥታ ለማጋራት የመረጧቸውን ነጋዴዎች ወይም ሌሎች ሦስተኛ ወገኖች የግላዊነት ወይም የደህንነት ተግባሮች በተመለከተ ኃላፊነት የለብንም። የግል መረጃዎን በቀጥታ ለማጋራት የመረጡት የማንኛውንም ሦስተኛ ወገን የግላዊነት መመሪያ እንዲገመግሙ እናበረታታዎታለን።

  የምንሰበስበው መረጃ፣ ከሦስተኛ አካላት የተገኘ መረጃን ጨምሮ፣ ለአጋሮቻችን ማለትም በGoogle LLC በባለቤትነት ለተያዙ ለሚተዳደሩ ኩባንያዎች ይጋራል። የገንዘብ ተቋማት ወይም ከዚያ ውጭ ሊሆኑ የሚችሉት አጋሮቻችን እንደዚህ አይነቱን መረጃ የዕለት ተዕለት የንግድ ስራቸውን ለማከናወን ይጠቀሙበታል።

  በGPC እና በአጋሮቹ መካከል የሚደረጉ የተወሰኑ ማጋራቶችን መርጠው እንዲተዉ መብት እንሰጥዎታለን። በግልጽ ለማስቀመጥ፣ የሚከተሉትን በምርጫዎ መተው ይችላሉ፦

  እንዲሁም ከGoogle LLC ወይም ጣቢያውን ወይም መተግበሪያውን ለጎበኙለት ሦስተኛ ወገን ነጋዴ መረጃ ከሚሰጡ አጋሮቻችን፣ ለዚያ ነጋዴ ክፍያ ለመፈጸም ጥቅም ላይ የሚውል Google Payments መለያ ያለዎት መሆኑን በምርጫዎ መተው ይችላሉ።

  ይህን በምርጫዎ ለመተው ከመረጡ፣ ምርጫዎን እንድንቀይረው እስከሚነግሩን ድረስ ተግባራዊ ይሆናል።

  የእርስዎን ብድር የመመለስ አቅም የሚመለከተው የግል መረጃዎ በGPC በአጋሮቹ መካከል እንዳይጋራ የሚፈልጉ ከሆነ፣ ወይም በእኛ የተሰበሰበውን የግል መረጃዎ አጋሮቻችን የሽያጭ ሃሳቦችን ለእርስዎ ለማቅረብ እንዲጠቀሙበት እንዲጋራላቸው የማይፈልጉ ከሆነ፣ ወይም Google LLC ወይም አጋሮቹ፣ ጣቢያውን ወይም መተግበሪያውን ለጎበኙለት የሦስተኛ ወገን ነጋዴ ክፍያ ለመፈጸም ጥቅም ላይ መዋል የሚችል የGoogle Payments መለያ ያለዎት መሆኑን በተመለከተ መረጃ እንዲያጋሩ የማይፈልጉ ከሆነ፣ እባክዎ ወደ መለያዎ በመግባት እና ወደ የGoogle Payments የግላዊነት ቅንብሮች ገጽ በመሄድ እና ምርጫዎችዎን በማዘመን ምርጫዎችዎን ያመልክቱ።

  በዚህ የግላዊነት ማስታወቂያ ከተገለጸው ውጭ የእርስዎን የግል መረጃ ከGPC ወይም ከአጋሮቻችን ውጭ ለሆነ ማንኛውም አካል አናጋራም። ከላይ በተብራራው መሰረት፣ Google Payments የGoogle መለያ ላላቸው የሚቀርብ ምርት ነው። በዚህ ማሳወቂያ ውስጥ የተመለከተው በምርጫ መውጣት ለGoogle መለያ ለመመዝገብ ለGoogle LLC በሚያቀርቡት ውሂብ ላይ ተጽዕኖ አይኖረውም።

  የመረጃ ደህንነት

  የደህንነት ተግባሮቻችንን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፣ እባክዎ ዋናውን የGoogle የግላዊነት መመሪያ ይመልከቱ።

  የGoogle Payments መለያዎ ደህንነት እርስዎ የመለያዎን የይለፍ ቃል(ሎች)፣ ፒኖች እና ሌሎች የአገልግሎቱን የመዳረሻ መረጃዎች በሚስጥር መያዝ ላይ ይወሰናል። የመለያዎን መረጃ ለሦስተኛ አካል ካጋሩ፣ ወደ መለያዎ እና የግል መረጃዎ መዳረሻ ይኖራቸዋል።

  የይለፍ ቃል(ሎች)ን እና/ወይም ፒን በምስጢር መያዝን እና ለማንም አለማጋራትን ጨምሮ፣ ተንቀሳቃሽ ስልክዎን እና በመሳሪያዎ ላይ የተጫኑ የGoogle Payments መተግበሪያዎን መዳረሻ መቆጣጠር የእርስዎ ኃላፊነት ነው። በተጨማሪም በGoogle Payments መተግበሪያ ውስጥ ያለው መረጃ ደህንነቱ ያልተረጋገጠ እንደሆነ ባመኑ ጊዜ ለGoogle ወይም ለሚመለከተው አጋር ማሳወቅም የእርስዎ ኃላፊነት ነው።

  © 2018 Google - Google መነሻ የGoogle የአገልግሎት ውሎች ቀዳሚ የግላዊነት ማሳወቂያዎች