የGoogle Payments የግላዊነት መመሪያ ለልጆች
ዕድሜዎን ይምረጡ፦ ዕድሜ ከ6-8 ዕድሜ ከ9-12
ዕድሜ 6-8
Google የእርስዎን የGoogle Payments ነገሮች እንዴት ደኅንነታቸው የተጠበቀ አድርጎ እንደሚያቆይ ማወቅ ይፈልጋሉ?
ይህ ገጽ ለልጆች ነው! Google መረጃዎን ለGoogle Payments እንዴት እንደሚጠቀምበት እና እንዴት ደኅንነቱን ጠብቆ እንደሚያቆየው ያሉ ጥያቄዎችን ይመልሳል።
ለወላጆች፦ ይህ መረጃ የሚመለከተው ከ13 ዓመት (ወይም በአገርዎ ውስጥ ከሚመለከተው ዕድሜ) በታች ለሆኑ ልጆች በFamily Link የሚተዳደሩ የGoogle መለያዎችን ብቻ ነው። ለተጨማሪ ዝርዝሮች የእኛን የግላዊነት ማስታወቂያ እና የግላዊነት መመሪያ ይመልከቱ።
Google ምን ዓይነት መረጃ ያስፈልገዋል?
ለሁሉም ምርቶች Google ከሚሰበስባቸው ነገሮች በተጨማሪም Google Payments በጥሩ ሁኔታ እንዲሠራ ከእርስዎ አንዳንድ መሠረታዊ መረጃን ያስፈልገናል።
የምዝገባ መረጃ
- የእርስዎ አድራሻ እና ስልክ ቁጥር
- የልደት ቀንዎ
- ስለ ክሬዲት ወይም ዴቢት ካርድዎ መረጃ
- ማን እንደሆኑ ለማረጋገጥ የሚያስችል መረጃ
አንዳንድ ጊዜ ሁሉም ነገር አስተማማኝ እና ደኅንነቱ የተጠበቀ መሆኑን ለማረጋገጥ ትንሽ ተጨማሪ መረጃ ልንጠይቅ እንችላለን።
ከሌሎች ቦታዎች የተገኘ መረጃ
- መደብሮች ላይ ስላሉ ክፍያዎችዎ መረጃ
- ስለ ባንክዎ እና የክሬዲት ወይም የዴቢት ካርድዎ መረጃ
የሆነ ነገር ሲገዙ መረጃ
- መቼ እና የት እንደገዙት እና ምን ያህል እንደነበር
- ክሬዲት ካርድ ወይም ዴቢት ካርድ ተጠቅመው እንደሆነ
Google የእኔን መረጃ ጥቅም ላይ የሚያውለው ምን ላይ ነው?
ለሁሉም ምርቶች Google መረጃዎን ከሚጠቀምባቸው መንገዶች በተጨማሪም እርስዎ የሚሰጡንን መረጃ እንደሚከተሉት ያሉ ነገሮችን ለGoogle Payments ለማድረግ እንጠቀምበታለን፦
- ክፍያዎችዎ ያለችግር እንዲጠናቀቁ ማገዝ
- የከፈሉትን ክፍያ ለእርስዎ እና ለወላጆችዎ ማሳየት
- ካስፈለገዎት ለወላጅዎ እገዛ መስጠት
- የእርስዎን መረጃ እና ገንዘብ ከመጥፎ ሰዎች ደኅንነቱ የተጠበቀ አድርጎ ለማቆየት ማገዝ
- የGoogle Payments ደንቦችን እየተከተሉ መሆኑን ማረጋገጥ
- የወደፊት ክፍያዎችዎ ደኅንነታቸው የተጠበቀ መሆን ወይም አለመሆኑን መወሰን
Google መረጃዬን ያጋራል?
ለሁሉም ምርቶች Google መረጃዎን ከሚያጋራባቸው መንገዶች በተጨማሪም Google Payments እንዲሠራ ለማድረግ መረጃዎን እንዲሁም ለሌሎች ልናጋራ እንችላለን። ጥቂት ምሳሌዎች እነሆ፦
- ሕጉ ትችላላችሁ ካለ
- መለያዎ እና ክፍያዎችዎ እየሠሩ እና ደኅንነታቸው ተጠብቆ ለማቆየት እንዲያግዝ
- ክፍያዎችዎ መፈጸማቸውን ማረጋገጥ
ወላጆቼ ምን ዓይነት ቁጥጥሮች አላቸው?
ወላጆችዎ ምን ማድረግ እንደሚችሉ እነሆ፦
- በGoogle Payments ላይ አዲስ ካርዶችን ለእርስዎ ማከል
- ካርዶችዎን ሲጠቀሙ እና ካርድ ሲወገድ ኢሜይሎችን ማግኘት
- ክፍያዎችዎን መመልከት እና በFamily Link ውስጥ የክፍያ ካርዶችን ማስወገድ
Google መረጃዬን ደኅንነቱ የተጠበቀ አድርጎ የሚያቆየው እንዴት ነው?
Google የመረጃዎን ደኅንነት ለመጠበቅ ለማገዝ ጠንክሮ ይሠራል። እርስዎ የይለፍ ቃላትዎን እና ፒኖችዎን በሚስጥር በመያዝ ማገዝ ይችላሉ።
ማስታወስ ያለብዎት አስፈላጊ ነገሮች፦
- መለያዎን ለማን እንደሚያጋሩ ይጠንቀቁ።
- መሳሪያዎን ማን እንዲጠቀም እንደሚፈቅዱ ይጠንቀቁ።
- የእርስዎ Google Payments ከእንግዲህ ደኅንነቱ የተጠበቀ እንዳልሆነ ካሰቡ ለወላጅዎ ይንገሩ።
ዕድሜ 9-12
Google Paymentsን ሲጠቀሙ ስለ ግላዊነትዎ ማወቅ ይፈልጋሉ?
ወደ ትክክለኛው ቦታ ነው የመጡት! መረጃዎን እንዴት እንደምንጠቀም እና ደኅንነቱን ጠብቆ ለማቆየት እንዴት እንደምናግዝ ያሉ በልጆች በብዛት የሚጠየቁ ጥያቄዎችን ያንብቡ።
ወላጆች፣ ይህ መረጃ የሚመለከተው ከ13 ዓመት (ወይም በአገርዎ ውስጥ ከሚመለከተው ዕድሜ) በታች ለሆኑ ልጆች በFamily Link የሚተዳደሩ የGoogle መለያዎችን ብቻ ነው። ለተጨማሪ ዝርዝሮች የእኛን የግላዊነት ማስታወቂያ እና የግላዊነት መመሪያ ይመልከቱ።
Google ምን ዓይነት መረጃ ያስፈልገዋል
?
ለሁሉም ምርቶች Google ከሚሰበስበው ነገር በተጨማሪም Google Payments ለእርስዎ የሚሠራ መሆኑን ለማረጋገጥ ሌላ መረጃ መጠየቅ ሊያስፈልገንም ይችላል።
የምዝገባ መረጃ
በGoogle መለያዎ ውስጥ የምናከማቸው አንዳንድ መረጃ እነሆ። አንዳንድ ውሂብ በመሣሪያዎ ላይ ሊከማች ይችላል።
- አድራሻ
- ስልክ ቁጥር
- የትውልድ ቀን
- የክሬዲት ወይም ዴቢት ካርድ መረጃ
- እንደ መታወቂያ ያለ ማንነትዎን የሚያረጋግጥ መረጃ
አንዳንድ ጊዜ ተጨማሪ መረጃ እንዲልኩልን ወይም መረጃዎን ወይም ማንነትዎን ለማረጋገጥ የሚረዱ ጥያቄዎችን እንዲመልሱ ልንጠይቅዎ እንችላለን።
ከሌሎች ቦታዎች የተገኘ መረጃ
ስለ እርስዎ መረጃ ከሌሎች ቦታዎች ልናገኝ እንችላለን፣ ለምሳሌ፦
- በመደብሮች ውስጥ ከGoogle Payments ግብይቶችዎ የተገኘ መረጃ
- የመክፈያ ዘዴዎችዎን እና መለያዎችዎን እንዴት እንደሚጠቀሙ በተመለከተ ከGoogle Payments ጋር ከተገናኙ ሌሎች ቦታዎች የተገኘ መረጃ
- የእርስዎ ባንክ ወይም ካርዱን የሰጠው አካል
- ከመክፈያ ዘዴዎ የሚገኙ ጥቅማጥቅሞች
- የእርስዎ መለያ እና ክፍያዎች ታማኝ መሆናቸውን ለማረጋገጥ እንዲያግዝ ክፍያዎችዎን በተመለከተ ከሌሎች ቦታዎች የተገኘ መረጃ
የሆነ ነገር ሲገዙ መረጃ
የሆነ ነገር ለመግዛት Google Paymentsን ሲጠቀሙ ስለ ግብይቱ መረጃ ልንሰበስብ እንችላለን፣ ለምሳሌ፦
- ቀን፣ ሰዓት እና መጠን
- የመደብሩ አካባቢ እና መግለጫ
- እንዴት እንደከፈሉ
Google የእኔን መረጃ ጥቅም ላይ የሚያውለው ምን ላይ ነው?
ለሁሉም ምርቶች Google መረጃዎን ከሚጠቀምባቸው መንገዶች በተጨማሪም እርስዎ የሚሰጡንን መረጃ እንደሚከተሉት ያሉ ነገሮችን ለማድረግ እንጠቀምበታለን፦
- በእርስዎ Google Payments (እንደ የደንበኛ አገልግሎት ያሉ) ላይ ችግሮች ካሉ የሆነ ሰው ወላጅዎን እንዲያግዝ ለማድረግ
- የእርስዎ፣ የሌሎች እና የGoogle ነገሮች ደህንነትን መረጃዎን ለመውሰድ ወይም ያለፈቃድዎ ገንዘብዎን ለማውጣት ሊሞክሩ ከሚችሉ ሰዎች ለመጠበቅ እንዲያግዝ
- መደብሮች ወይም ሌሎች ኩባንያዎች እርስዎ የጠየቋቸውን ነገሮች እንዲሰጡዎት ለማገዝ
- እርስዎ የGoogle Payments ደንቦችን እየተከተሉ መሆኑን ለማረጋገጥ
- ስለወደፊቱ የGoogle Payments ግብይቶችዎ ውሳኔ ለማሳለፍ
- የመክፈያ ዘዴዎ ስለሚያደርጋቸው ሌሎች አሪፍ ነገሮች ማወቅዎን ለማረጋገጥ
የሚሰጡንን መረጃ የGoogle Payments አገልግሎትን እስከተጠቀሙ ድረስ ልናቆይ እንችላለን፣ እና ሕጉን መከተል ካስፈለገን ደግሞ ረዘም ላለ ጊዜም ልናቆየው እንችላለን።
Google መረጃዬን ያጋራል?
ለሁሉም ምርቶች Google መረጃዎን ከሚያጋራባቸው መንገዶች በተጨማሪም መረጃዎን ከGoogle ውጭ ላሉ ሌሎች ሰዎች ልናጋራው የምንችልባቸው ምክንያቶች ጥቂት ብቻ ናቸው፣ ለምሳሌ፦
- ሕጉ እንደምንችል ከነገረን
- መለያዎን እያሄደ እንዳለ ለማቆየት ግዢዎችዎ መጠናቀቃቸውን ለማረጋገጥ፣ የመለያዎን ደኅንነት ለማሻሻል፣ እርስዎን ሊሰርቅዎት ወይም ሊያታልልዎት ከሚሞክር ሰው ለመጠበቅ ወይም ለዕለታዊ ሥራችን
- የመክፈያ ዘዴዎ ደኅንነቱ የተጠበቀ እና አሁንም እንደሚሠራ ለማረጋገጥ እንዲያግዝ
- በሌሎች ቦታዎች ለሚቀርብ አገልግሎት የተጠየቀውን ምዝገባዎ ለማጠናቀቅ
Google ሌሎች አንዳንድ ኩባንያዎችን በባለቤትነት ይይዛል ወይም ይቆጣጠራል። አንዳንድ ጊዜ ለዕለታዊ ንግዳቸው ካስፈለጋቸው መረጃዎን ለእነሱ እናጋራለን። ይህ እንደ እርስዎ የሚሸምቱባቸው መደብሮች ካሉ ሌሎች ቦታዎች ልናገኝ የምንችለውን ማንኛውንም መረጃ ያካትታል።
ወላጆቼ ምን ዓይነት ቁጥጥሮች አላቸው?
ወላጅዎ ምን ማድረግ እንደሚችሉ እነሆ፦
- ለሚታከለው እያንዳንዱ የክፍያ ካርድ በአካል ማጽደቅ
- ካርዶችዎን ሲጠቀሙ እና ካርድ ሲወገድ ኢሜይሎችን ማግኘት
- በFamily Link ውስጥ የGoogle Payments ግብይቶችዎን መገምገም እና የክፍያ ካርዶችን ማስወገድ
Google Pay መረጃዬን ደኅንነቱ የተጠበቀ አድርጎ የሚያቆየው እንዴት ነው?
Google የእርስዎን ደኅንነት ለመጠበቅ ብዙ ያደርጋል፣ ነገር ግን እርስዎ የመለያዎን የይለፍ ቃላት፣ ፒኖች እና ሌላ አስፈላጊ መረጃን በሚስጥር መያዝዎ አስፈላጊ ነው።
ልብ ይበሉ፦
- የGoogle መለያ መረጃዎን ለሌሎች ቦታዎች ካጋሩ የGoogle ክፍያዎች መገለጫዎ እና የግል መረጃዎ መዳረሻ ይኖራቸዋል
- የእርስዎን መሣሪያ ወይም የGoogle Wallet መተግበሪያ ማን እንዲደርስባቸው እንደሚፈቅዱ ይጠንቀቁ
የGoogle Wallet መተግበሪያዎ ደኅንነቱ የተጠበቀ እንዳልሆነ ካሰቡ ለGoogle እንዲያሳውቁ ወላጅዎን እገዛ ይጠይቁ።
መጨረሻ የተዘመነው፦ ማርች 16፣ 2026
© 2026 Google – Google የGoogle አገልግሎት ውል ቀዳሚ የግላዊነት ማስታወቂያዎች