Google Payments የግላዊነት ማስታወቂያ

ለመጨረሻ ጊዜ የተሻሻለው፡ ማርች 28፣ 2022

Google የግላዊነት መመሪያ እርስዎ በGoogle ምርቶችና አገልግሎቶች በሚጠቀሙበት ጊዜ የግል መረጃዎን እንዴት እንደምንይዘው ያብራራል። ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ተጠቃሚ ከሆኑ፣ ተጨማሪ መረጃዎችን በGoogle የታዳጊ ግላዊነት መመሪያ ውስጥ ማግኘት ይችላሉ። Google Payments ለGoogle መለያ ባለቤቶች የቀረበ ሲሆን፣ አጠቃቀምዎም በGoogle የግላዊነት መመሪያ ተገዢ በመሆን ነው። በተጨማሪም፣ ይህ የግላዊነት ማስታወቂያ ለGoogle Payments ልዩ የሆኑ የGoogle የግል ተግባሮችን ያብራራል።

የእርስዎ የGoogle Payments አጠቃቀም በGoogle Payments የአገልግሎት ውል የሚመራ ነው፣ ይህም በዚህ የግላዊነት ማስታወቂያ የተገለጹትን አገልግሎቶች በበለጠ ያብራራል። በዚህ የGoogle Payments የግላዊነት ማስታወቂያ ውስጥ ያልተብራሩት በእንግሊዝኛ ዓብይ ፊደላት የተጻፉት ቃላት በGoogle Payments የአገልግሎት ውል ውስጥ የተገለጸውን ትርጉማቸውን ይይዛሉ።

የGoogle Payments የግላዊነት ማስታወቂያ Google Payment ኮርፖሬሽንን («GPC») ጨምሮ በGoogle LLC ወይም በድርጅት ጉዳዮች ሙሉ ባለቤትነት በተያዙ ኩባንያዎች ለሚሰጡ አገልግሎቶች ተግባራዊ የሚሆን ነው። አገልግሎቱን የሚሰጠው የትኛው በሌላ ድርጅት የሚተዳደር አገልግሎት አቅራቢ እንደሆነ ለማወቅ እባክዎ ከአገልግሎቱ ጋር የቀረበልዎትን የGoogle Payments የአገልግሎት ውል ይመልከቱ። በአውሮፓ ኢኮኖሚያዊ አካባቢ (ዩናይትድ ኪንግደምን ሳያካትት) ለምትኖሩ ተጠቃሚዎች (በGoogle የገበያ ቦታ ላይ ከሚሸጡት በስተቀር)፣ ኃላፊነት ያለበት የመረጃዎ የውሂብ ተቆጣጣሪ Google Ireland Limited ነው። በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ለምትኖሩ ተጠቃሚዎች (በGoogle የገበያ ቦታ ላይ ከሚሸጡት በስተቀር)፣ ኃላፊነት ያለው የመረጃዎ የውሂብ ተቆጣጣሪ Google LLC ነው። እርስዎ ዩናይትድ ኪንግደምን ሳይጨምር በአውሮፓ ኢኮኖሚያዊ አካባቢ የሚኖሩ ከሆነ እና በGoogle የገበያ ቦታ ላይ የሚሸጡ ከሆነ፣ ለእርስዎ መረጃ ኃላፊነት ያለው የውሂብ ተቆጣጣሪ የGoogle Payment Ireland Limited ነው። ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ የሚኖሩ ከሆነ እና በGoogle የገበያ ቦታ ላይ የሚሸጡ ከሆነ፣ ለእርስዎ መረጃ ኃላፊነት ያለው የውሂብ ተቆጣጣሪ Google Payment Limited ነው። ብራዚል ውስጥ ለምትኖሩ ተጠቃሚዎች፣ ለመረጃዎ ኃላፊነት ያለው የውሂብ ተቆጣጣሪ Google LLC ሲሆን የብራዚል ሕግ አስገዳጅ በሚሆንበት ሁኔታ Google Brasil Pagamentos Ltda ሊሆን ይችላል።

የምንሰበስበው መረጃ

Google የግላዊነት መመሪያ ውስጥ ከተዘረዘረው መረጃ በተጨማሪ የሚከተሉትንም ልንሰበስብ እንችላለን፦

የሰበሰብነውን መረጃ እንዴት እንደምንጠቀምበት

Google የግላዊነት መመሪያ ከተዘረዘሩት አጠቃቀሞች በተጨማሪ፣ ለእኛ እና ለGPC ወይም በሥራችን ለሚተዳደሩ ሌሎች ድርጅቶች ያቀረቡልንን መረጃ እንዲሁም ስለእርስዎ ከሦስተኛ ወገኖች የተገኘን መረጃ የGoogle Paymentsን ለደንበኞች አገልግሎት ዓላማ እንድናቀርብልዎ፣ እና መብቶችን፣ ንብረቶችን ወይም የGoogle ደህንነቶችን ከጉዳት ለመጠበቅ እንዲሁም ተጠቃሚዎቻችን፣ ወይም ህዝቡ፣ ማጭበርበርን፣ ማስገርን ወይም ሌላ መጥፎ ባህርይን መከላከልን ለማገዝ ያካትታል። በተጨማሪም እንደዚህ ዓይነት መረጃ ሦስተኛ ወገኖች እንዲያቀርቡልዎት የጠየቋቸውን ምርቶችና አገልግሎቶች ለማቅረብ እንዲችሉ ለማገዝ ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል። እንዲሁም የመለያውን ውሎች በማክበር የቀጠሉ መሆኑን ለማወቅ፣ የወደፊት የGoogle Payments ግብይቶችዎን በተመለከተ ውሳኔ ለመወሰን፣ እንዲሁም በእርስዎ የተጠየቁ የGoogle Payments ግብይቶችን ለሚመለከቱ አግባብነት ያላቸው የንግድ ፍላጎቶች የGoogle Payments መለያዎን ለመገምገም መረጃውን እንጠቀምበታለን።

የምዝገባ መረጃዎ ከGoogle መለያዎ ጋር በመያያዝ ይቀመጣል እንዲሁም የመክፈያ ዘዴ ምዝገባዎ በGoogle አገልጋዮች ላይ ይቀመጣል። በተጨማሪም፣ የተወሰኑ የውሂብ ክፍሎች በተንቀሳቃሽ ስልክዎ ላይ ሊቀመጡ ይችላሉ። ያቀረቡትን መረጃ የሕግ ሂደትን እና የቁጥጥር ግዴታዎችን ለማክበር ለተራዘመ ጊዜ ልናቆየው እንችላለን።

የምናጋራው መረጃ

በሚከተሉት ሁኔታዎች ብቻ የእርስዎን መረጃ ከGoogle ውጭ ላሉ ሌሎች ኩባንያዎች ወይም ግለሰቦች ልናጋራ እንችላለን፦

ለምሳሌ፣ Google Payments በመጠቀም ግዢ ወይም ግብይት በፈጸሙ ጊዜ፣ ግዢ ለሚፈጽሙለት ወይም ለሚገበያዩት ኩባንያ ወይም ግለሰብ እርስዎን የሚመለከቱ የተወሰኑ የግል መረጃዎችን ልናቀርብ እንችላለን። ይህም በGoogle Play ላይ ግዢ ለመፈጸም Google Payments በሚጠቀሙበት ጊዜ ግዢ ለሚፈጽሙለት ገንቢ የግል መረጃዎን ማጋራትን ያካትታል። በተጨማሪም በ«Google Pay ይግዙ»ን ወይም ተመሳሳይ አዝራርን በመጠቀም ክፍያ ሲያስጀምሩ፣ ነጋዴው የዘመነ የግዢ መረጃ (ለምሳሌ ግብር፣ የማስረከቢያ ወጪዎች እና ሌላ የዋጋ መረጃ) ለማስላት እና ነጋዴው ያንን የመክፈያ ዓይነት ከእርስዎ መቀበል መቻሉን እንዲሁም ለግዢዎ ጥቅም ላይ የሚውለውን የመክፈያ ዘዴ በማስመልከት የሚኖሩ ጥቅማጥቅሞችን ወይም ገደቦችን ለመለየት እንዲችል የእርስዎን ዚፕ ኮድ ወይም ፖስታል ኮድ እና የመክፈያ ዓይነት የሚመለከት መረጃ ለነጋዴው ድር ጣቢያ ወይም መተግበሪያ መላክን ሊያካትት ይችላል። የሦስተኛ ወገን ክፍያ ወደ Google Payments መለያዎ ሲያክሉ፣ የተወሰኑ እርስዎን የሚመለከቱ የግል መረጃዎችን፣ ለምሳሌ የእርስዎ ስም፣ የመገለጫ ምስል፣ ኢሜይል፣ አይፒ እና የሂሳብ መጠየቂያ አድራሻ፣ ስልክ ቁጥር፣ የመሣሪያ መረጃ፣ አካባቢ እና የGoogle መለያ እንቅስቃሴ መረጃ የመሳሰሉትን አገልግሎቱን ለመስጠት እንደ አስፈላጊነቱ ከሦስተኛ ወገን የክፍያ አቅራቢው ጋር ልንለዋወጥ እንችላለን።

የተሳታፊ ነጋዴን ጣቢያ ወይም መተግበሪያ ሲጎበኙ፣ በጣቢያዎች ወይም በመተግበሪያዎች ጥቅም ላይ መዋል የማይችሉ ባህሪያትን የማየት ዕድልዎን ለመቀነስ በነጋዴው ጣቢያ ወይም መተግበሪያ ግዢ ለመፈጸም የሚያስችል የGoogle Payments መለያ ጥቅም ላይ መዋል ከሚችል የመክፈያ ዘዴ ጋር እንዳለዎት ነጋዴው ሊያረጋግጥ ይችላል።

በቀጥታ ለሦስተኛ ወገን ነጋዴ ድር ጣቢያ ወይም መተግበሪያ የሚያቀርቡት ማንኛውም መረጃ በዚህ የግላዊነት ማስታወቂያ አይሸፈንም። የግል መረጃዎን በቀጥታ ለማጋራት የመረጧቸውን ነጋዴዎች ወይም ሌሎች ሦስተኛ ወገኖች የግላዊነት ወይም የደህንነት ተግባሮች በተመለከተ ኃላፊነት የለብንም። የግል መረጃዎን በቀጥታ ለማጋራት የመረጡት የማንኛውንም ሦስተኛ ወገን የግላዊነት መመሪያ እንዲገመግሙ እናበረታታዎታለን።

የምንሰበስበው መረጃ፣ ከሦስተኛ ወገኖች የተገኘ መረጃን ጨምሮ፣ ከአጋሮቻችን፣ ማለትም በGoogle LLC በባለቤትነት በተያዙ እና በሚተዳደሩ ኩባንያዎች የተጋራ ነው። አጋሮቻችን፣ የገንዘብ ተቋማት ወይም ከዚያ ውጭ ሊሆኑ ይችላሉ፣ እንደዚህ አይነቱን መረጃ የዕለት ተዕለት የንግድ ሥራቸውን ለማከናወን ይጠቀሙበታል።

በGPC እና በአጋሮቹ መካከል የሚደረጉ የተወሰኑ ማጋራቶችን መርጠው እንዲተው መብት እንሰጥዎታለን። በግልፅ ለማስቀመጥ፣ የሚከተሉትን በምርጫዎ መተው ይችላሉ፦

በተጨማሪም ጣቢያውን ወይም መተግበሪያውን ለጎበኙለት ሦስተኛ ወገን ነጋዴ በዚያ ነጋዴ ጣቢያ ወይም መተግበሪያ ላይ ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል የGoogle Payments መለያ ያለዎት መሆኑን በማሳወቅ ከGoogle LLC ወይም አጋሮቹ መርጠው መውጣትን መምረጥ ይችላሉ።

ይህን በምርጫዎ ለመተው ከመረጡ፣ ምርጫዎን እንድንቀይረው እስከሚነግሩን ድረስ ተግባራዊ ይሆናል።

የእርስዎን ብድር የመመለስ አቅም የሚመለከተው የግል መረጃዎ በGPC እና በአጋሮቹ መካከል እንዳይጋራ የሚፈልጉ ከሆነ ወይም በእኛ የተሰበሰበውን የግል መረጃዎ አጋሮቻችን የሽያጭ ሃሳቦችን ለእርስዎ ለማቅረብ እንዲጠቀሙበት እንዲጋራላቸው የማይፈልጉ ከሆነ ወይም Google LLC ወይም አጋሮቹ፣ ጣቢያውን ወይም መተግበሪያውን ለጎበኙለት የሦስተኛ ወገን ነጋዴ የGoogle Payments መለያ ያለዎት መሆኑን መረጃ እንዲያጋሩ የማይፈልጉ ከሆነ፣ እባክዎ ወደ መለያዎ በመግባት፣ ወደ የGoogle Payments የግላዊነት ቅንብሮች ገፅ በመሄድ እና ምርጫዎችዎን በማዘመን ፍላጎትዎን ያመልክቱ።

በዚህ የግላዊነት ማሳወቂያ ወይም በGoogle የግላዊነት መመሪያ ውስጥ ከተገለጸው ውጭ የእርስዎን የግል መረጃ ከGPC ወይም ከአጋሮቻችን ውጭ ለሆነ ለማንኛውም አካል አናጋራም። ከላይ በተብራራው መሰረት፣ Google Payments የGoogle መለያ ላላቸው የሚቀርብ ምርት ነው። በዚህ የግላዊነት ማሳወቂያ ውስጥ የተመለከተው በምርጫ መውጣት ለGoogle መለያ ለመመዝገብ ለGoogle LLC በሚያቀርቡት ውሂብ ላይ ተጽዕኖ አይኖረውም።

የመረጃ ደህንነት

የደህንነት ተግባሮቻችንን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፣ እባክዎ ዋናውን የGoogle የግላዊነት መመሪያይመልከቱ።

የGoogle Payments መለያዎ ደህንነት እርስዎ የመለያዎን የይለፍ ቃል(ሎች)፣ ፒኖች እና ሌሎች የአገልግሎቱን የመዳረሻ መረጃዎች በሚስጥር መያዝ ላይ ይወሰናል። የመለያዎን መረጃ ለሦስተኛ አካል ከአጋሩ፣ እሱ ወይም እሷ ወደ መለያዎ እና የግል መረጃዎ መዳረሻ ይኖራቸዋል።

የይለፍ ቃል(ሎች)ን እና/ወይም ፒን በምስጢር መያዝን እና ለማንም አለማጋራትን ጨምሮ፣ ተንቀሳቃሽ ስልክዎን እና በመሣሪያዎ ላይ የተጫኑ የGoogle Payments መተግበሪያዎን መዳረሻ መቆጣጠር የእርስዎ ኃላፊነት ነው። በተጨማሪም በGoogle Payments መተግበሪያ ውስጥ ያለው መረጃ ደህንነቱ ያልተረጋገጠ እንደሆነ ባመኑ ጊዜ ለGoogle ወይም ለሚመለከተው አጋር ማሳወቅም የእርስዎ ኃላፊነት ነው።

© 2020 Google – Google Home የGoogle የአገልግሎት ውል ቀዳሚ የግላዊነት ማስታወቂያ